image
image
image
image
image

የልደታ ክ/ከተማ ፍትህ ፅ/ቤት የህግ ስርፀት ዉል ረቂቅ ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት በሰው መነገድና ሰዉን በህገ ወጥ መልኩ ድንበር ማሻገር ወንጀልን መከላከል እና መቆጣጠር የህግ ማእቀፎች ላይ ለወጣት እና ለሴት ማህበር ስልጠና ሰጠ።

መስከረም 24 .2018, 2018
ዳይሬክቶሬቱ በሰው መነገድና ሰዉን በህገ ወጥ መልኩ ድንበር ማሻገር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣዉን አዋጅ ቁጥር 1178/2012 እና ወንጀሉን ለመከላከል ከወጡት ሌሎች የህግ ማእቀፎች ላይ ስልጠናውን የሰጠዉ። ስልጠናዉን የሰጡት የህግ ስርፀት ዉል ረቂቅ ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ህግ ዮናታን አብደላ በሰዉ መነገድና ሰዉን በህገ ወጥ መልኩ ድንበር ማሻገር ወንጀል ወጣቱን እና አምራች የሆነዉን ትዉልድ ለወንጀሉ ሰለባ በማድረግ በአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ቀዉሶችን እንደሚያስከትል በስልጠናው ተገልፆል። ከዚህ ጋር ተያይዞ ሁሉም ህብረተሰብ ወንጀሉን ለመከላከል መረባረብ እንዳለበት አፅንኦት ተሰጥቷል ። በስልጠናዉ ላይ ከአሰልጣኞች ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቷል ።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች