በልደታ ክ/ከተማ የፍትህ ጽ/ቤት ዋና ዋና አገልግሎቶች
- 1.በፍትሐብሔር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የሚሰጡ አገልግሎቶች
- የፍትሐብሔር ጉዳዩችን ወይም ኮንስትራክሽን ክርክር መወሰን፣ ማስወሰን እና ማስፈጸም
- አማራጭ የክርክር መፍቻ ዘዴ እንዲፈታ ማድረግ
- የህግ አገልግሎት ለተፈቀደላቸውና ክርክር ለሚያደርጉ ተቋማት ድጋፍና ክትትል ማድረግ
- የደንብ ጥሰት ቅጣት ማስፈፀም
- 2. የወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የሚሰጡ አገልግሎቶች
- የወንጀል ጉዳዮች የመመርመርና ውሳኔ መስጠት አገልግሎት
- የወንጀል ቀጥታ ክስ፣ ይግባኝና ሰበር መመስረትና መከራከር አገልግሎት
- ለሰብዓዊ መብት ጥሰት ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ ጉዳዮችን በመለየት የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ድጋፍ ያደርጋል፡፡
- በመሰረታዊ የሠብዓዊ መብት ዙሪያ ግንዘቤ በመስጠት የሚሰጡ አገልግሎቶች የዜጎችን የሠብዓዊ መብት ያከበሩ እንዲሆኑ ድጋፍ ያደርጋል፡፡
- 3. በህግ ስርፀት ውል ረቂቅና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት የሚሰጡ አገልግሎቶች
- የህግ ስርፀት አገልግሎት
- የህግ ምክር አገልግሎት
- የውል ረቂቅ ዝግጅት አገልግሎት
- የህግ አገልግሎት ለተፈቀደላቸዉና በራሳቸው ክርክር ለሚያደርጉ እና ለማያደርጉ ተቋማት ድጋፍና ክትትል ማድረግ አገልግሎት
- አስተዳደራዊ ውሳኔዎች ከህግ ጋር የተጣጣመ መሆኑን ማረጋገጥ አገልግሎት