image
image
image
image
image

"መብትና ግዴታውን የሚያውቅ ተማሪ መፍጠር ለሀገር ግንባታው ትልቅ ሚና አለው ።" ልደታ ክፍለ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት

የካቲት 22, 2018
የልደታ ክፍለ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤ በክፍለ ከተማው ስር ላሉ ከአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለተውጣጡ መምህራንና ተማሪዎች በመሠረታዊ ህጎች ዙሪያ ስልጠና ሰጠ። በወቅቱ የትምህርት ቤት የሚኒ ሚዲያ ተወካይ መምህርና ሚኒ ሚዲያ ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎች የስልጠናው ተሳታፊ ሆነዋል ። የልደታ ክፍለ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤ ኃላፊ አቶ ጋሻዬነህ ታፈሰ በመክፈቻ ንግግራቸው መብትና ግዴታውን የሚያውቅ ተማሪ መፍጠር ለሀገር ግንባታው ትልቅ ሚና አለው በማለት ከተማችን በከፍተኛ ፍጥነት በሁሉም ዘርፍ እያደገች ትገኛለች በማለት በቀጣይ እንደትኩረት ትኩረት አቅጣጫ የተያዘው የፍትሕ ስርዓቱን ማሻሻል በመሆኑ በሐገሪቱ ተፈጻሚነት ያላቸውን ሕጎች የማሳወቅ ስራ ይሰራል ብለዋል። ኃላፊው አክለውም የስልጠናው ዋነ አላማ ብለው ያሉት የነገ ሀገር ተረካቢ ተማሪዎች መሰረታዊ በሆኑ ህጎች ዙሪያ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እና በለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸው በሚገጥማቸው ማህበራዊ ጉዳይ ላይ መብትና ግዴታቸውን እንዲያውቁ ነው ብለዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች