image
image
image
image
image

በሴቶች መብት ዙሪያ በብሔራዊ የሴቶች ፖሊሲና በህግ ማእቀፎች ጥበቃ የተደረገላቸውን መብቶች መነሻ በማድረግ ለሴት ማህበር አባለት ስልጠና ተሰጠ።

ጥቅምት 7, 2018
የልደታ ክፍለ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት የህግ ስርፀት ውል ረቂቅ እና ምክር መስጠት ዳሬክቶሬት ከ10ሩ ወረዳ የሴት ማህበር ለተውጣጡ አባላት ግንዛቤ ሰጥቷል። በመድረኩ ብሔራዊ የሴቶች ፖሊሲና በህግ ማእቀፎች ዙሪያ የስልጠና ሰነድ ለሰልጣኞች ቀርቧል። የልደታ ክፍለ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወርቁ ከተማ ስልጠናውን ሲከፍቱ የሴቶችን መብት ለማክበርና ለማስጠበቅ የተደረጉት አለምና አህጉር አቀፍ ስምምነቶችን ስንመለከት በሴቶች ላይ አለም አቀፋዊ በሆነ ሁኔታ መድሎ ይፈፀም እንደነበር የሚያሰይ ነው በማለት ይህን ፆታን መሰረት ያደረገ መድሎ ለማስወገድ እና የሴቶችን እኩልነት ለማረጋገጥ ለመጠበቅ የተለያዩ አለም አቀፍ ስምምነቶች ተደርገዋል ሲሉ ገልፀዋል። ሀገራችን ኢትዮጵያም የሴቶች ብሔራዊ ፖሊሲ በማውጣት እና የህግ ማዕቀፍ በማዘጋጀት ስራ ላይ እንደምትገኝ የገለፁት አቶ ወርቁ በዚህ መሰረት የሴቶችን መብት ማክበር የሁሉንም ማህበረሰብ መብት ማክበር ነው ሲሉ ጠቅሰዋል። የሴቶችን መብትና ደህንነት በማስጠበቅ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባ የገለፁት አቶ ወርቁ አያይዘው የሴቶችን መብትና ደህንነታቸውንም ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ፖሊሲዎች ህጎችን ተፈፃሚነት ለማረጋገጥ ሁሉም ግንዛቤው ኖሮት የየድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል። የሴቶች መብት ከመሠረቱ መጠበቅና ማስጠበቅ የሀገር ልማትና ሁለንተናዊ እድገት ላይ ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው በማለት አቶ ወርቁ ገልፀዋል። የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው ሴቶችን መብትና ደህንነት እንዲረጋገጥ የበኩላችንን ድርሻ እንወጣለን ብለው ስልጠናውም መብትና ደህንነታቸውን ለማስጠበቅ አቅም ይሆነናል ሲሉ ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች