image
image
image
image
image

የልደታ ክ/ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት የህግ ስርፀት ዉል ረቂቅ ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ከሁሉም ወረዳዎች የተወጣጡ የማህበረሰብ ክፍል ስልጠና ሰጠ።

ጥቅምት 30, 2018
በስልጠናው የተሳተፉ አረጋዊያን የእድር ማህበሮች እና ባለድርሻ አካላት ለአረጋውያን በወጡ የህግ ማዕቀፎች ላይ ስልጠና ተሰጠ። በስልጠናው ንግግር ያደረጉት የልደታ ክ/ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ወርቁ ከተማ እንደተናገሩት አረጋዊያን በህብረተሰባችን ትልቅ ቦታ የሚሰጣቸዉ የትዉልድ ተምሳሌት እና ሀብት መሆናቸዉን በመግለፅ መብታቸዉን ማስጠበቅ እና የፍትህ አካላት ሀላፊነት መሆኑን ገልፀዋል። በስልጠናዉ ላይ የፍትህ ሚኒስቴር የልደታ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ አሰፋ በፍትህ ሚኒስቴር በኩል ብዙ ስራዎች እንደሚሰሩ እና የአረጋውያንን መብት በማስጠበቅ ረገድ ሁሉም በየደረጃው የራሱን ሚና እንደሚወጣ ገልፀዋል። ስልጠናዉን የሰጡልን ዐቃቤ ህግ ወ/ሮ አልጋነሽ ገ/ስላሴ የአረጋውያን የፅንሰ ሀሳብ ምንነት የአረጋውያን መሰረታዊ ችግሮች ከስነ ልቦና የማህበራዊ ችግሮች እና ችግሮችን ለመቅረፍ ምን መደረግ አለበት በሚለዉ ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን የአረጋውያን መብቶች ከህጉ አንፃር ስልጠና ተሰቷል። በስልጠናዉ መጨረሻ ከተሳታፊዎች የተነሱት ጥያቄዎች ላይ ማብራሪያ ተሰጥቷል ።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች