image
image
image
image
image

የወንዝ ዳርቻ ልማት እና ብክለት ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ ለልደታ ክ/ከተማ ምክር ቤት ስር ለሚገኙ ቋሚ ኮሚቴ አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

ሰኔ 9, 2018
የልደታ ክፍለ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት የህግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት የወንዝ ዳርቻ ልማት እና ብክለት ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ ለልደታ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት ስር ለሚገኙ ቋሚ ኮሚቴ አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ። አዲስ አበባ በተለያዩ ዘርፎችና የልማት እንቅስቃሴዎች ከፍተኛ ለውጥ እያመጣች መሆኑ ይታወቃል።ይህንን የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ቀጣይነት እንዲኖረው ለውጡን የሚመጥንና ለውጡን ሊያስቀጥል የሚችል አዋጆች ደንቦችና መመሪያዎች እየወጡ መሆኑ ግልፅ ነው።ከእነዚህ ደንቦች ውስጥ የወንዝ ዳርቻ ልማትና ብክለትን ለመከላከል የወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ይጠቀሳል ። የአዲስ አበባ የውሃ አካላት በተለያዩ ሰው ሰራሽ ምክንያቶች በጥራትም ሆነ በመጠን ጉዳት እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ይታወቃል። ይህ ሰው ሰራሽ የሆነ ድርጊት በሰውና በእንስሳት ላይ የከፋ ጉዳት እያስከተለ በመሆኑና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም በከተማዋ የማሚገኙ ወንዞችን በማልማት ለነዋሪዎቿ ምቹና የመዝናኛ ማዕከል እንዲሆኑ እያደረገ ይገኛል ይህንን የወንዝ ዳርቻ ልማት ዘላቂነቱን ለማረጋገጥና ወንዞች ከበካይነት ወደ መዝናኛነት ለማሸጋገር ይህ ደንብ መውጣቱን በስልጠናው ላይ ተነስቷል። ሰልጣኞቹም እንደ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴነተሠቸው ይህ ደንብ ከማህበረሰቡ ጋር በሚኖራቸው የዕለት ተዕለት ግንኙነት ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ ትልቅ አቅም እንደሆናቸው ገልፀዋል

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች