image
image
image
image
image

በሰው መነገድና ሰውን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወንጀሉ ተሳትፎ ያላቸውን አካላት የህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማስቻል በተቀናጀ አግባብ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

ግንቦት 16, 2018
የልደታ ክፍለ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት "ህገወጥና ኢ-መደበኛ ፍልሰትን በጋራ እንከላከል" በሚል መሪ ቃል 3 መደበኛ ጉባኤ አካሄደ በሰው መነገድና ሰውን በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን መከላከል እና መቆጣጠር ምክር ቤት የ2017 በጀት ዓመት 3 መደበኛ ጉባኤ አካሄ። የአዲስ አበባ ከተማ ፍትህ ቢሮ ሀላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ በምክር ቤት ጉባኤ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ሰውን መነገድና በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል አስከፊነት በመረዳት በአገር ደረጃ ተፈፃሚነት ያለው አዋጅ በማውጣትና በርካታ አደረጃጀቶችን በማደራጀት ተግባራትን በመስራት ለውጦችን ማምጣት ተችሏል በማለት ህገ ወጥ የሰዎች ዝወውርን ለመከላከልና ወንጀለኞችን የህግ ተጠያቂ ለማድረግ የተቀናጀ ስራ እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል። የህዝባችንን ንቃተ ህሊና ለማዳበር ግንዛቤ የመፍጠር ተግባር በሰፊው እየተሰራ ነው ያሉት አቶ ተክሌ በዛብህ ማህበረሰብ ግንዛቤ እንዲኖረው በማድረግ ከህገወጥ የሰዎች ዝውውር እራሱን መቆጠብ እንደሚገባ በመድረኩ አንስተዋል። የችግሩን ውስብስብነት በዜጎች ህይወትና አካል ላይ የሚያደርሰው አስከፊነት በመረዳት በአገር ደረጃ ትኩረት ተሰጥጦት እስከ ታች አደረጃጀቶችን በመፍጠር በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ገልፀው ሁሉም የበኩሉን ሀላፊነት ሊወጣ ይገባል ሲሉ አቶ ተክሌ በዛብ አንስተዋል የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ በማጠቃለያ ንግግራቸው እንደተናገሩት የህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ በምክር ቤት አባላት የተሰራው ስራ ቀላል አይደለም በማለት በተሻለ አግባባ ግንዛቤ በመፍጠር ዜጎችን የመታደግ ተግባር በሰፊው እየተሰራ ነው ሲሉ ተናግረዋል። በሰው መነገድና ሠውን በህገ-ወጥ ድንበር ማሻገርን መከላከል ላይ መንግስት ትኩረት በመስጠት የህግ ማዕቀፍ ተበጅቶለት እየሠራ ነው ያሉት ወ/ሮ አበባ እሸቴ አያይዘው ከህግ አካላቱ ጋር ተሳስረን በመስራት ውጤታማ ተግባር እንሰራለን ነው በማለት ገልፀዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ም/ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ነፃነት ደረሰ የህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ችግር ታሳቢ ባደረገ መልኩ እስከ ወረዳ የሚወርድ መዋቅር በመዘርጋት በሰዎች መነገድና ህገ-ወጥ ስደትን ለመከላከል ቅንጅታዊ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልፀዋል በህገ ወጥ ደላሎች ዜጎቻችን እንዳይታለሉ እንግልት እንዳይደርስባቸው ሰፊ ግንዛቤ መፍጠር ያስፈልጋል ያሉት ወ/ሮ ነፃነት አያይዘው ዜጎችቻችን በሚፈጠሩ የስራ አማራጮች እንዲጠቀሙ በቅንጅት መስራት ያስፈልገናል ሲሉ ተናግረዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ጋሻዬነህ ታፈሰ በሰዎች ላይ ኢ-መደኛ የሆነ ድርጊት ሲከወን የነበረ ሲሆን ይህን ወንጀል ድርጊት ለመከላከል አዋጅ ደንብ በማውጣትና ለማህበረሰብ ግንዛቤ በመስጠት ዜጎችን ከዚህ ድርጊት እንዲቆጠብ የማድረግ ስራ እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል። በሰው የመነገድ ተግባርን መቆጣጠርና መከላከል ላይ የምክር -ቤት አባላትም የግንዛቤና የህግ ማስከበር ሚናችሁን ለመወጣት የነቃ ተሳትፎ ማድረግ ይገባል በማለት አቶ ጋሻዬነህ አንስተዋል። የምክር ቤቱ ተሳታፊዎችም በሰው የመነገድና በህገ ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከል የሁሉም ዜጋ ድርሻ እንደሆነ በማንሳት ምክር ቤቱ አባላትም የተሰጣቸውን ሀላፊነት መወጣት ይገባቸዋል በማለት አንስተዋል።።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች