image
image
image
image
image

ልደታ ክ/ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት ባቋቋማቸው የህግ ክበባት ሰብሳቢ መምህራን ና የክበብ አባላት ጋር የፓናል ውይይትና ስልጠና ሰቷል።

ጥቅምት 24, 2018
ስልጠናውን የሰጠው ልደታ ክ/ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት የህግ ስርጸት ውል ረቂቅና ምክር መስጠጥ ዳይሬክቶሬት ሲሆን መድረኩን የከፈቱት |የልደታ ክ/ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ወርቁ ከተማ በ 2017 የበጀት አመት ካቋቋማቸው የንቃተ ህግ ክበባት በማስፋትና ቁጥራቸውን በመጨመር በ 2018 የበጀት አመት በህግ ክበባት በኩል ንቃተ ህግ ሲፈጠር እደቆየ ገልጸዋል፡፡ ጽ/ቤት ሃላፊው አክለውም የንቃተህግ ክበባትን ማቋቋም አንዱ የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ማሳኪያ ማእቀፍ የሆነና ህግን አክባሪ፣ መብትና ግዴታውን የሚያውቅ፣ ሰላማዊና ነገን ተረካቢ ትቅልድ ከመፍጠር አንጻር የጎላ ሚና እንዳለው ገልጸዋል፡፡ በፓናል ውይቱቱም ተሳታፊዎች የዚህ የህግ ትራንስፈፐርሜሽን እንቅስቃሴ ተግባራዊነት ላይ ያጋጠማቸውን ችገር፣የሚያስፈልጉ ድጋፎችንና ጥያቅዎችን በማንሳት ለውይይት ያቀረቡ ሲሆን በመድረኩ የጋራ መግባባት ላይ መድረስ ተችሏል፡፡ ከውይይቱ በተጨመሪ በመሰረታዊ ህግና ፍትህ ቢሮ ባወጣው የንቃተ ህግ ክበብ ማቋቋሚያ ማኑዋል ዙሪያ ዐቃቤ ህግ ዮናታን አብደላ ስልጠና ሰተዋል፡፡ስልጠናውም ተማሪዎች በሚገባቸውና በሚረዱት መልኩ ግንዛቤ የወሰዱ ከመሆኑም በተጨማሪ ስል ህግ ክብብ ዝርዝር የአሰራር ሁኔታዎችን ስልጠና ያገኙበት ነው፡፡ በቀጣይም ወጥነት ያለው የሪፖርት፣የመረጃ ኣያያዝና የድጋፍና ክትትል ስርአት ተዘርግቶ እንደሚሰራ በመድረኩ ገለጻ ተደርጓል፡፡

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች