image
image
image
image
image

የልደታ ክ/ከተማ ፍትህ ፅ/ቤት በመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 87/2017 ላይ ስልጠና ሰጠ።

ጥቅምት 28, 2018
በበለጥሻቸዉ ጤና ጣቢያ በመገኘት ስልጠናዉን በቀን 20/02/2018 እና 21/02/2018 የተሰጠ ሲሆን በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር በማድረግ ስልጠናዉን ያስጀመሩት የልደታ ክ/ከተማ ፍትህ ፅ/ቤት የህግ ስርፀት ዉል ረቂቅ ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዐቃቤ ህግ ኤሚሊያ ፍሬድሪክ አዋጅ ቁጥር 87/2017 ሲወጣ ያካተታቸዉን አዳዲስ ድንጋጌዎች ለመንግሥት ሰራተኛዉ ግንዛቤ እንዲኖረዉ ከማስቻል ረገድ የስልጠናው አስፈላጊነት በመግለፅ መብቱን የሚያዉቅ እና ግዴታዉን የሚወጣ ሰራተኛ ከማፍራት ረገድ ጉልህ ጠቀሜታ እንዳለዉ ተገልጿል ። ስልጠናዉን የሰጡልን አቃቤ ህግ ሞቲ ተስፋዬ ስልጠና አዋጅ ቁጥር 87/2017 ያካተታቸዉ ድንጋጌዎች በማብራራት ስልጠናዉ የተሰጠ ሲሆን በመጨረሻም ከሰልጣኞች ለተነሱት ምላሽ ተሰጥቷል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች