• Vision

    የጽ/ቤቱ ራዕይ

    በ2022 በኢትዮጵያ የፍትሕ ተቋማት ተምሣሌት ሆኖ ማየት ነው፡፡

  • Mission

    የጽ/ቤቱ ተልዕኮ

    የፍትሐብሔር እና የወንጀል ጉዳዮችን በመወሰን እና በማስወሰን ፤ ህግን በማስረፅ እና ምክር በመስጠት፤ የህግ ረቂቅ ጥናትና ምርምር በማድረግ፤ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀልን ለመከላከል ማስተባበር እና የሰብዓዊ መብቶች ድርጊት መርሐ ግብርን በማስተግበር የከተማ አስተዳደሩ እና የነዋሪውን መብትና ጥቅም ማስጠበቅ፡፡

  • Assets

    የጽ/ቤቱ እሴቶች

    ግልፅነት:- የሚሰጡ አገልግሎቶች ግልፀኝነትን መርሕ ያደረገ ይሆናሉ ፣

    ተጠያቂነት:- በሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ ተጠያቂነትን ማስፈን ፣

    ፍትሐዊነት:- ያለአድሎ መስራት ፣

    የሕግ የበላይነት:- በሕግ መሰረት መስራት ፣

    ሙያዊ ብቃት:- ክህሎትን መሰረት ያደረገ አገልግሎት መስጠት ፣

    ስነ ምግባር:- ሙያው የሚፈለገውን ስነምግባር መላበስ ፣

    ትብብርና አጋርነት:- ቅንጅታዊ አሰራር መከተል ፣

    ሙያዊ እና ተቋማዊ ነፃነት:- በገለልተኝነት እና ከተፅዕኖ ነፃ ሆኖ ማገልገል