#

አቃቤ-ህግ ዮሴፍ ካሳሁን
የወንጀል ጉዳዮች ክርክር ዳይሬክቶሬት

14 June 2025

የዳይሬክተሩ መልዕክት

ዳይሬክቶሬቱ በበጀት አመቱ ተልዕኮውን ለመወጣት እንዲችል ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል፡፡ በዋነኛነት አበይት ተግባራትን ከማሳካት አኳያ የህግ የበላይነትን ለማስከበር ብሎም የህዝብ መብት እና ጥቅም ለማስከበር በወንጀል ጉዳዮች ደንብ መተላለፍ/petty offence/፣ በግል አቤቱታ የሚቀርቡ ወንጀሎች እና የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ላይ ትኩረት በመስጠት ስራውን እያከናወነ ይገኛል፡፡

በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ስር 9 ፖሊስ ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆን የወንጀል ጉዳዮች ክርክር ዳይሬክቶሬት በነዚሁ 9 ፖሊስ ጣቢያና መምሪያው ጨምሮ ዐቃቤ ሕጎችን በየጣቢያው በመመደብ ከፖሊስ ጋር በጋራ በመሆን የወንጀል የምርመራ ሂደቱን በበላይነት በመምራት ስራውን እያከናወነ ይገኛል፡፡ በግል አቤቱታ የሚቀርቡ ወንጀሎች በባህሪያቸው ቀላል ከመሆናቸው የተነሳ የግል ተበዳይና ተከሳሽ ዘላቂ ግንኙነታቸው እንዳይሻክር ለማድረግ ሲባል ጉዳያቸውን በእርቅ እንዲጨርሱ ከፍተኛ ጥረት ይደረጋል፡፡

በተጨማሪም ዳይሬክቶሬቱ የዜጎችን የሠብዓዊ መብት አያያዝና አጠባበቅ ላይ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን በሰብዓዊ መብት ዙሪያ ከሚሰራቸው ስራዎች መካከል የተጠረጠሩና በቁጥጥር ስር የሚገኙ ዜጎች የሰብዓዊ መብት አያያዛቸውን በተመለከተ በየሳምንቱ ዓርብ ዓርብ በፖሊስ ጣቢያዎችና በመምሪያውም ጭምር የእስረኞች ጉብኝት የሚደረግ ሲሆን በዚሁም ጉብኝት የተጠረጠሩና የተያዙ ሰዎች በፍርድ ቤት መጥሪያ የተያዙ ስለመሆናቸው፣ በ48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት ስለመቅረባቸው፣እና መሰል የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች የተከበሩ መሆናቸውን የምንከታተል ሲሆን ለሰብዓዊ መብት ጥሰት ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ ጉዳዮችን በመለየት የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ድጋፍ ያደርጋል፡

ዳይሬክቶሬቱ በልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኙ ጽ/ቤቶቸ የሠብዓዊ መብት ድርጊት መርሀ ግብር ፎካል ፐርሶችን እንዲወክሉ በማስደረግና ለፎካል ፐርሰኖቹ በመሰረታዊ የሠብዓዊ መብት ዙሪያ ግንዘቤ በመስጠት በየጽ/ቤታቸው የሚሰጡ አገልግሎቶች የዜጎችን የሠብዓዊ መብት ያከበሩ እንዲሆኑ ድጋፍ እንዲሰጡ ለማድረግ ተችሏል፡፡ በአጠቃላይ የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ጽ/ቤት የወንጀል ጉዳይች ክርክር ዳይሬክቶሬት የሕግ የበላይነትን ከማስጠበቅ አንፃር ፣ የዜጎች ፍትሕ የማግኘት መብትን ከማስከበርና የሠብዓዊ መብትን ከመከታተል አንፃር ዘርፈ ብዙ ስራዎችን የሚያከናውን ዳይሬክቶሬት ነው፡፡

በዳይሬክቶሬቱ የሚሰጡ የአገልግሎት አይነቶች

የወንጀል ጉዳዮች የመመርመርና ውሳኔ መስጠት አገልግሎት ፣

ከተገልጋይ የሚጠበቅ ቅድመ ሁኔታ

• የምርመራ ወይም የአቤቱታ መዝገብ

• ማስረጃዎች

የወንጀል ቀጥታ ክስ፣ ይግባኝና ሰበር መመስረትና መከራከር አገልግሎት ፣

ከተገልጋይ የሚጠበቅ ቅድመ ሁኔታ

• ለአቃቤ ህጉ አቤቱታ ማቅረብ

• ይግባኝ ይደረግልኝ ጥያቄ በደብዳቤ መቀበል

መልዕክትዎን ይላኩ