#

አቃቤ-ህግ ልሳኑ ክብሩ
የፍታብሔር ክርክር ዳይሬክቶሬት

14 June 2025

የዳይሬክተሩ መልዕክት

በፍ/ክርክር ዳይሬክቶሬት የህዝብን ጥቅም/ public interest/ለማስጠበቅ ክርክር የምናደርግ ሲሆን በዋናነት ከመንግስት ቤት እንዲሁም በተወሰኑ መዝገቦች ደግሞ ከመንግስት ፕሮጀክት ከሼድ ጋር የተያያዙ ክርክሮችን የምናደርግ ሲሆን ከመንግስት ቤት ጋር ተያይዞ የመኖሪያ ቤት የማግኘት መብት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለዜጎች ጥቅም ላይ እንዲውል የመንግስት ቤቶች ከሚተላለፍባቸው አሰራሮች ውጪ ከተያያዙ ውሎች ሲቋረጡ የመኖሪያ ቤት እንዳላቸው በማረጋገጥ ውል ሲያቋርጡ የሚቀርቡ ክሶችን በመከላከል ቤቶቹ ለታለመላቸው አላማ እንዲውሉ ማስቻል አንድ በዳይሬክቶሬቱ የምናከናውነው ተግባር ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ከፕሮጀክት ጋር ተያይዞ በግምት የሚነሱ የግል ይዞታቸው በሚያቀርቧቸው የሁከት ክሶች እና እግድ ለማስነሳት ተገቢው ክርክር ማድረግ እና የስራ እድል ፈጠራ ጋር ተያይዞ ፍትሃዊ የሆነ የሀብት አጠቃቀም እንዲኖር ይሄ ውል ጊዜ ካበቃ በኋላ ሊቋረጥ የሚቀርቡ ክሶች በመከላከል ህዝብ ጥቅም የምናስጠብቅበት አግባብ ነው ያለው ከፍታብሔር ክርክሮች በተጨማሪ አስተዳደራዊ ቅጣት የሚፈፀምባቸውን ጥፋቶችንም በተመለከተ ድርጊቱን የፈፀሙ አካላት ሳይፈፅሙ ሲቀሩ በአቃቢህግ ክስ በማቅረብ ጤናማ እና ምቹ አካባቢ በመፍጠር ረገድ ፤ያጋጠሙ ችግሮች ቢኖርም ጥፋተኞች እንዲቀጡ እና ሌሎች እንዲማሩ ለማድረግ በአጠቃላይ ስራዎችን ውጤታማ እና በብቃት ለመወጣት የፓናል ውይይቶች እና በጋራ ውሳኔ መሰረት ውጤታማ ክርክር እንዲደረግ ወይም የማያዋጡ በክርክሮችን በማቋረጥ ውጤታማ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

በዳይሬክቶሬቱ የሚሰጡ የአገልግሎት አይነቶች

የፍትሐብሔር ጉዳዩችን ወይም ኮንስትራክሽን ክርክር መወሰን፣ ማስወሰን እና ማስፈጸም

ከተገልጋይ የሚጠበቅ ቅድመ ሁኔታ

• የተከሰሰበትን ክስ

• ክስ እንዲመሰረትለት ደብዳቤ

• ለክሱ የሚረዱ ማስረጃዎች

አማራጭ የክርክር መፍቻ ዘዴ እንዲፈታ ማድረግ ፣

ከተገልጋይ የሚጠበቅ ቅድመ ሁኔታ

• ደብዳቤ

የህግ አገልግሎት ለተፈቀደላቸውና ክርክር ለሚያደርጉ ተቋማት ድጋፍና ክትትል ማድረግ ፣

ከተገልጋይ የሚጠበቅ ቅድመ ሁኔታ

• ድጋፍ የሚፈልጉበትን ለይቶ ማቅረብ፣

የደንብ ጥሰት ቅጣት ማስፈፀም

ከተገልጋይ የሚጠበቅ ቅድመ ሁኔታ

• የተከሰሰበትን ክስ

• ክስ እንዲመሰረትለት ደብዳቤ

• ለክሱ የሚረዱ ማስረጃዎች

መልዕክትዎን ይላኩ