#

አቃቤ-ህግ ኤሚሊያ ፍሬድርክ
የህግ ስርፀት ውል ረቂቅና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር

14 June 2025

የዳይሬክተሩ መልዕክት

በልደታ ክ/ከተማ ፍትህ ፅ/ቤት በህግ ስርፀትና ውል ረቂቅና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት ውስጥ በዋናነት በማህበረሰቡ ላይ በህግ ላይ ያላቸውን ንቃተ ህግ ማሳደግ በዋነኝነት በዳይሬክቶሬቱ የሚሰራ ተግባር ነው፡፡ በንቃተ ህግ ስራው በዋነኝነት የህብረተሰቡን ችግር ፈቺዎች እና ወቅታዊ በሆኑ የህግ ጉዳዮች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ይሰራል፡፡ ከህግ ስርፀት ተግባራቱም በተጨማሪም በዳይሬክቶሬቱ ከሚሰሩት ተግባራት መካከል ነፃ የህግ ምክር መስጠት ነው ይህንንም ስንል ህብረተሰቡ/ተገልጋዩ/ በእለት ተእለት ኑሮ ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮች እነዚህንም ችግሮች ከህግ አግባብ እንዴት መፍትሄ መስጠት ይቻላል የሚለውን በምክር መልክ የሚሰጥ ሲሆን የህግ ምክር በፅሁፍ እንዲሁም በቃል የሚሰጥ ሲሆን ተገልጋዩ ለመገልገል ሲመጣ በመረጠው አግባብ የህግ ምክር የምንሰጥ ሲሆን፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በስርፀት ዳይሬክቶሬት የውል ረቂቅ እና ከውል አስተያየት ጋር ተያይዞ የሚሰሩ ስራዎች አሉ፡፡ በአዋጅ ቁጥር 84/2016 አንቀፅ 25 ንኡስ አንቀፅ 6 መሰረት ለፍትህ ፅ/ቤት በተሰጠው ስልጣን መሰረት የአስፈፃሚ አካላት የሚያደርጉትን ውል የመመርመር እና ህጋዊነታቸውን የማረጋጋጥ ስልጣን የተሰጠው ሲሆን በተሰጠው ስልጣን መሰረት የመንግስት መ/ቤቶች የሚያደርጓቸውን ውሎች በመመርመር እና እንዲሁም ደግሞ የውል ረቂቅ አዘጋጅቶ በመስጠት እና ከዚህም በተጨማሪ ደግሞ ውል ከተዋዋሉ በኋላ ተፈፃሚነታቸውን በማረጋገጥ የመንግስትን ሀብትና ንብረት ከብክነት ለማዳን ፅ/ቤቱ በዳይሬክቶሬቱ በኩል ይሰራል፡፡

በዳይሬክቶሬቱ በዋናነት ከላይ የተመለከትናቸውን ተግባራት የሚከናወኑ ሲሆን ከዛም በተጨማሪ በዳይሬክቶሬቱ ብሮሸሮችን የማዘጋጀት እና የማሰራጨት ስራዎችን ይሰራል፡፡ ከዚህም በተጨማሪም በአዋጅ ቁጥር 84/2016 መሰረት በተሰጠው ስልጣን በመመርኮዝ በክ/ከተማው የሚሰጠው አስተዳደራዊ ውሳኔዎች ከህግ ጋር የተጣጣመ መሆኑን ያረጋገጣል እንዲሁም የማስተካከያ እርምጃዎች ይወስዳል እንዲወሰድም ያደርጋል፡፡ይህንንም ስልን በመንግስት መ/ቤቶች የሚሰጡ አስተዳደራዊ ውሳኔዎችን ከአስተዳደር ስነ ስርአት ህጉ አዋጅ ቁጥር 1183/2012 መሰረት ውሳኔ እየተሰጡ መሆናቸውን ማረጋጋጥ ነው፡፡ በዚህም መሰረት ውሳኔ በሚሰጥበት ጊዜ በፅሁፍ መሆን እንዳለበት፡ ቃለ ጉባኤ መያዝ እንዳለበት እና ሌሎች አካሄዶችን መከተል እንዳለባቸው ከመንግስት መስሪያ ቤቶች በአካል በመሄድ ድጋፍና ክትትል በማድረግ እንዲሁም ግብረ መልስ በመስጠት ማስተካከል ያለባቸውን ነገሮች በግብረ መልስ መልኩ በመስጠት የሚከናወን ተግባር ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በዳይሬክቶሬቱ በሰው መነገድና ሰዎችን በህገወጥ መልኩ ድንበር ማሻገር ወንጀል ለመከላከልና ለመቆጣጠር በከተማው አቅጣጫ በወረደው መሰረት ወንጀሉን ለመከላከል ከትብብር ጥምረት ጋር በመተባበር የተለያዩ ስራዎች ከግንዛቤ ከመስጠት ብሮሸሮችን ከመበተን የአደባባይ ቅስቀሳዎችን በማድረግ እና ህብረተሰቡ ሴቶች ወጣቶች በወንጀሉ ላይ ግንዛቤ መፍጠር ስራዎችን አጠናክረን በዳይሬክቶሬቱ የሚሰሩት ተግባራት ናቸው፡፡የህግ ስርፀት ዳይሬክቶሬት ብዙ በሚባል መልኩ አስተዋፆ ያደርጋል ይህንንም ስንል በዳይሬክቶሬቱ ያሉ ዐ/ህግ ዋነኛ ተግባራቸው ቀደም ሲልም የተገለፀበት አግባብ አለ ስልጠና መስጠት ነው ስለዚህ ለህብረተሰቡ እና ስልጠና ለሚፈልግ ተቋም ስልጠና መስጠት ብቻም ሳይሆን በፅ/ቤታችን ያሉትንም ዐ/ህጎች በተለያየ ከስራቸው ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ጉዳዮች እና አዳዲስ ህጎችም በሚወጡበት ጊዜ ለፅ/ቤቱ ዐ/ህጎች ስልጠና በመስጠት የህግ ስርፀት ተግባሩን ያከናውናል ‘’የራስዋ አሮባት የሰው ታማስላለች’’ የሚለው አባባል በኛ ፅ/ቤት ላይ እንዳይሰራ ማህበረሰቡን ከማስረፅ በፊት የመንግስትን እና የህዝብን መዝገብ ይዞ የሚከራከረው ዐ/ህግ በህጉ በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው ማስቻል በዳይሬክቶሬቱ ለፅ/ቤቱ ስኬታማነት አስተዋፆ የሚያደርግ መሆኑ ነው፡፡

በዳይሬክቶሬቱ የሚሰጡ የአገልግሎት አይነቶች

የህግ ስርፀት አገልግሎት ፣

ከተገልጋይ የሚጠበቅ ቅድመ ሁኔታ

• የስልጠና ጥያቄ/ በደብዳቤ

የህግ ምክር አገልግሎት ፣

ከተገልጋይ የሚጠበቅ ቅድመ ሁኔታ

• ምክር የሚሰጥበትን ጉዳይ

• ደብዳቤ

• በአካል ወይም በስልክ

የውል ረቂቅ ዝግጅት አገልግሎት፣

ከተገልጋይ የሚጠበቅ ቅድመ ሁኔታ

• የተዘጋጀውን ረቂቅ መመሪያ

• ዉል እንዲዘጋጅለት ርዕሰ ጉዳዩ በደብዳቤ መላክ

የህግ አገልግሎት ለተፈቀደላቸዉና በራሳቸው ክርክር ለሚያደርጉ እና ለማያደርጉ ተቋማት ድጋፍና ክትትል ማድረግ አገልግሎት

ከተገልጋይ የሚጠበቅ ቅድመ ሁኔታ

• ክትትልን ድጋፍ እንዲደረግለት የሚፈልገውን ጉዳይ ገልፆ ደብዳቤ

አስተዳደራዊ ውሳኔዎች ከህግ ጋር የተጣጣመ መሆኑን ማረጋገጥ አገልግሎት

ከተገልጋይ የሚጠበቅ ቅድመ ሁኔታ

• ውሳኔ ይጣራልኝ ጥያቄ

መልዕክትዎን ይላኩ