`

የዜጎች የስምምነት ሰነድ |
Citizens Charter

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2014 ዓ.ም የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትን መልሶ ለማደራጀት በወጣ አዋጅ ቁጥር 74/2014 መሰረት ፍትህ ቢሮ እንደገና የተቋቋመ ሲሆን ከተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት መነሻ ለተ የልደታ ክፍለ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት እየተከናወኑ ያሉ የለውጥ ሂደቱን ቀጣይነት ለማረጋገጥ፣ የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመፍታት ቢሮው በሚሰጠው አገልግሎት ላይ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው የአሰራር ስርዓትን በዘላቂነት ለማስፈን እንዲችሉ፣ ቢሮው የተሰጡትን ተግባራት እና ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስችሉ ስልቶች ነድፎ የተገልጋዩን ፍላጎት የማርካት ስራ ለመስራት፣ እያንዳንዱ አገልግሎት የሚወስደውን ጊዜ መጠን አውቆ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ስራ ለመስራት፣ የአገልግሎት አይነቱን መለየትና ደንበኞች ማሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታ አዉቀዉ ተገቢዉን አገልግሎት ማግኘት ይችሉ ዘንድ ይህ የዜጎች የስምምነት ሰነድ ተዘጋጅቷል፡፡

የዜጎች ስምምነት ሰነድ ዓላማ

  1. የልደታ ክፍለ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት በሕግ በተሰጠው ስልጣንና ሀላፊነት መሰረት ለተገልጋዩ የሚሰጡ አገልግሎቶች በመሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ ጥናት ስታንዳርድ መሰረት እንዲሰጥ ለማድረግ፣ በስታንዳርዱ መሰረት አገልግሎት በማይሰጡ አካላት ላይ ተጠያቂነትን ለማስፈን የሚረዳ የዜጎች የስምምነት ሰነድ በማዘጋጀት የመልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን በዘላቂነት መፍታት ነዉ፡፡

የዜጐች የስምምነት ሰነድ አስፈላጊነት

  1. በፍትሕ ጽ/ቤት ስር ያሉ ዳይሬክቶሬቶች በሚያቀርቡት የአገልግሎት አይነትና የጥራት ደረጃን ከተገልጋዩ ህብረተሰብ ጋር በመወያየትና የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ወደ ተግባር ለመግባት የሚያስችል ግልፅ የሆነ ቃል የሚገቡበት አሰራር ባለመኖሩ ይሄንን ግልፅ ማድረግ በማስፈለጉ፣
  2. በአገልግሎት ሰጭውና በአገልግሎት ተቀባዩ መካከል የመተማመን ፣የመግባባትንና አብሮ የመስራት ባህልን የሚያዳብር በመሆኑና የሚሰጡ አገልግሎቶችን የጥራት ደረጃ ማስጠበቅ በማስፈለጉ፣
  3. በፍትሕ ጽ/ቤት ስር የሚገኙ ጽ/ቤቶች እና ዳይሬክቶሬቶች በሚሰጡት አገልግሎቶች የሚጠበቅባቸውን ግዴታ ለህዝቡ ግልፅ በሆነ መንገድ የሚያሳውቁበት እንዲሁም አገልግሎቱን ለማግኘት ከተገልጋዮች ምን እንደሚጠበቅ /የተገልጋዮችን መብት እና ግዴታ/ የሚያሳይ የአሰራር ስርአት መዘርጋት በማስፈላጉ
  4. የቅሬታ አቀባበልና አፈታት ሥርዓትን ለማሻሻል፣ ተገልጋዮች የመገልገል መብታቸዉን ማረጋገጥ እንዲችሉ፣

የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት

    የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት በዝርዝር ለማወቅ ከፈለጉ ይህን Duties and Responsibility ይጫኑ

የተገልጋዮች መብት

  1. ህግ ረቂቅ፣ ንቃተ ህግና ምክር የማግኘት፣
  2. ተደራሽና ቀልጣፋ የሆነ ፍትህ የማግኘት፣
  3. በክብር የመስተናገድና አድሎ የሌለበት አገልግሎት የማግኘት፣
  4. ስለ አገልግሎቱ ሙሉ መረጃና የተቋሙን ዕቅድና አፈፃፀም ሪፖርቶች የማግኘት፤ እንዲሁም በዕቅድ ዝግጅት ውይይትና በዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረኮች ላይ የመሳተፍ ፣
  5. ቅሬታ የማቅረብ፣ በጹሁፍ ወይም በቃል ምላሽ የማግኘት፤
  6. በቂና ወቅታዊ ምላሽ ባላገኙበት ጊዜ በየደረጃው ለተቋቋሙት የቅሬታ ማስተናገጃ ክፍሎችና ኃላፊዎች ቅሬታና አቤቱታ የማቅረብ ፣
  7. በቢሮው እና በክ/ከተማ ፍትህ ጽ/ቤቶች በሚያካሂዱት የምዘናና የእውቅና አሰጣጥ ሥርዓት እንዲሁም በዕቅድ ዝግጅት ውይይትና በአፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ላይ የመሳተፍ መብት አለው፡፡

የተገልጋዮች ግዴታዎች

  1. ትክክለኛ መረጃዎችንና ማስረጃዎች የማቅረብ ፣
  2. የአገልግሎት ሰጪ ተቋሙን ህግና ሥርዓትን የማክበር፣
  3. አገልግሎት ሰጪ ተቋሙ ተገልጋዩን በጋራ በሚከናወኑ ተግባራት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ በጠየቀው ጊዜ ድርሻውን የመወጣት ግዴታ አለበት፡፡

የተቋሙ ግዴታ

  1. አገልግሎቱን ለመስጠት የሚያስፈልጉ ግብአቶች አሟልቶ መገኘት፣
  2. በተቀመጠው የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ መሰረት በክብር የማስተናገድ፤
  3. ለተገልጋዮች ፍትሃዊ፤ አድሎ የሌለበት አገልግሎት የመስጠትና በእኩልነት የማገልገል፣
  4. ቅሬታና አስተያየት ለመቀበልና ለመፍታት የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት የመዘርጋት፤
  5. ለሚቀርቡ ቅሬታዎችና አቤቱታዎች ፍትሀዊና ፈጣን ምላሽ የመስጠት፤
  6. ለተገልዮች የተቋሙን ዕቅድና የአፈፃፀም ሪፖርት ግልፅ ማድረግ አለበት፤
  7. በዜጎች የስምምነት ሰነድ መሰረት ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል አስፈላጊ ግብዓቶችን የማሟላትና ተቋማዊ አቅም የመገንባት ግዴታ አለበት፡፡