Welcome to Lideta Subcity Justice Office!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ እዉነተኛ ፍትህ ⚖️ ለሰፈነባት እና ተምሳሌት ለሆነች ልደታ ይተጋል!

የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት

የልደታ ክ/ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት ከሚያከናውናቸው ዋና ዋና ተግባራት መካከል የክፍለ ከተማው ማህበረሰብ እንዲሁም የአስተዳደሩ ፅ/ቤቶች በህግ ንቃተ ህሊና ዙሪያ፤ የህግ ምክር ድጋፍ እና በፍትሀ ብሄር ክርክር የህዝብና መንግስት ሀብት ጥቅም ማስጠበቅ ሲሆን ህግን ጠንቅቆ አለማወቅ ሊያስከትል ከሚችል ጉዳት ማህበረሰቡን እና አስተዳደሩን ለመጠበቅ በህግ አግባብ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል፡፡ በዚህም በርካታ ሀብትና ንብረት አለአግባብ እንዳይባክን ሰፊ ስራ ተሰርቷል፡፡

ወቅቱን ያማከለ የህግ ግንዛቤ መሰረት በማድረግ በብሮሸር፤ በሰሌዳ መፅሄት፡ በራዲዮ እንዲሁም በቴሌቪዥን እና በአዲስ ልሳን ጋዜጣ የህግ አምድ በማውጣት ለክ/ከተማው እና ለከተማ አስተዳደሩ ግንዛቤ የሚሰጥ ሲሆን በተጨማሪም የህግ ንቃተ ህሊናን በማሳደግ ደረጃ በተለያየ ጊዜ መጠይቆችን በመበተን እና ማህበረሰቡ ሊያውቀው ይገባል ተብሎ የሚታሰበውን የህግ ጉዳዮች የማስጨበጥ ስራ ሰርተናል፡፡ በመንግስት ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 87/2017 ላይ፤ የቤት አከራይ ተከራይ አዋጅ 1320/2016 አዋጅን እና ሌሎችም ተጨባጭ ብዙ የሚባሉ የህግ ግንዛቤ ማሳደጊያ መድረኮችን በማዘጋጀት በተለይ የህግ ንቃተ ህሊና የማሳደግ ስራ ሰርተናል፡፡... ተጨማሪ ያንብቡ

አቶ ወርቁ ከተማ , የልደታ ክ/ከተማ ፍትሕ ጽ/ቤት ኃላፊ
image description

የልደታ ክ/ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልደታ ክ/ከተማ የፍትህ ጽ/ቤት ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መነሻ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትና የለውጥ ሥራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በብቃቱና እና በሥነ-ምግባሩ የተመሰገነ የሰው ኃይል እንዲመራ በማድረግ ለተገልጋዮቹ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በአዲስ መልክ በመለየት አደራጅቷል፡፡

በተጨማሪም በጽ/ቤት የሚሰጠው አገልግሎት የተገልጋይ ፍላጎትን ማዕከል አድርጎ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን ለማስቻል የሚሰጡ የአገልግሎት አይነቶች፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበት ስታንዳርድ፣ የሚሰጥበትን ቦታ እና ከተገልጋይ የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎችን በግልጽ በዝርዝር በማስቀመጥ የጽ/ቤቱ ሠራተኞች በተቀመጠላቸው ስታንዳርድ መሰረት ፍህታዊና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡና ተገልጋዮች ምን ዓይነት አገልግሎት በምን ዓይነት ደረጃ ማግኘት እንደሚገባቸው ግንዛቤ በመፍጠር በዚህም ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲኖር፣ በህዝብና መንግስት መካከል መተማመን እንዲፈጠር፣ ልማትና ዲሞክራሲ እንዲያብብ ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ በመሆኑም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂት ለመፍታት በምናደርገው ጥረት ባለድርሻ አካላትና ህብረተሱቡ ከጽ/ቤቱ ጎን እንዲቆሙ እናሳስባለን፡፡

ጥያቄ ካልዎት እባክዎ ለመደወል አያመንቱ ወይም ይጎብኙን!!

+251118659432
+251974555843

አድራሻችን:-

የልደታ አስተዳደር ህንጻ 7ኛ ወለል ቢሮ ቁ 705
የስራ ሰዓት ከሰኞ - አርብ ከጠዋቱ 2፡30 - ቀኑ 11፡30